ቢኒያም ማርቆስ
በግል የሚሠራ መተግበሪያ · አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያበትክክል የሚሰራ እና በማንኛውም ሰዓት በቀላሉ በሚያገኙት ባለሙያ የተገነባ ድህረ ገጽ ወይም ሲስተም።
ከስራው በኋላ እልም ብለው እንደሚጠፉ ባለሙያዎች አይደለሁም፤ የውጭ ኤጀንሲዎች የሚያባክኑት ጊዜና የቋንቋ እንቅፋት አይኖርም። የንግድዎን ድህረ ገጽ ወይም ሶፍትዌር እራሴ በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ እቀርጻለሁ፣ እገነባለሁ፣ ቀጣይነት ያለው ድጋፍም እሰጣለሁ።
የቅርብ ጊዜ ስራዎች
እንዴት ልረዳዎት እችላለሁ?
ከአንድ ቀላል ድረ-ገጽ አንስቶ እስከ ረጅም ጊዜ ትብብር ድረስ፣ አብረን ለመስራት ሶስት አማራጮች አሉን።
የንግድ ድረ-ገጽ
በዲጂታል ዓለም ውስጥ እራስዎን የሚያሳይ፣ ደንበኞችን የሚስብልዎ፣ እና ስራዎን በሚገባው መልኩ የሚያቀርብ ድረ-ገጽ።
ለንግድዎ የተሰራ ሲስተም
ከወረቀትና ከኤክሴል ተላቀቁ — በስራ ገበታዎ ሁሉንም ነገር በቀላሉ እንዲቆጣጠሩ የሚረዳ ስራዎ እንዴት እንደሚሄድ በመረዳት የተሰራ ሶፍትዌር።
ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና እንደአስፈላጊነታቸው ማሻሻያዎች
ሲስተምዎ ሁል ጊዜ እንዲሰራ፣ እንዲዘመን፣ እና እየተሻሻለ እንዲሄድ እንከታተላለን — አዲስ ሰው መቅጠር ሳያስፈልግዎ።
እንዴት አብረን ልንሰራ እንችላለን?
ፕሮፖዛል
ስራው ምን እንደሚሸፍን፣ ደረጃ በደረጃ እንዴት እንደሚሰራ፣ እና እስከ መቼ እንደሚደርስ የሚገልጽ ዋጋ ያገኛሉ።
ግንባታ
ስራው እየተሰራ ባለበት ጊዜ ሁሉ፣ ስራው እንዴት እየሄደ እንዳለ በየጊዜው አሳውቅዎታለሁ — ስራው እይተሰራ እስከየት እንደደረሰ ለማየት የሚችሉበትን የሙከራ ማስፈንጠርያ(link) ይኖርዎታል።
ማስረከብ
ስራው ወደ ኦንላይን ይወጣል፣ ሙሉ ቁጥጥር ለእርስዎ ይሰጣል፣ እንዲሁም ለተወሰነ ጊዜ (በስምምነታችን በሚግለጽው የእይታ ጊዜ ቆይታ) የሚታዩ ስህተቶችን እናስተካክላለን።